Amharic English
አማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

ሚድያና ኩነቶች ያግኙን ክፍት የሥራ ቦታ ስለ እኛ
አማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

አግምኢ
ቀዳሚ ገጽ
የምርምር ዘርፎች
ኃብትና ሕትመቶች
Publications/ Journal
Research MS/ ARMS
ARARI: About us

ስለ እኛ




እንኳን ወደ አማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ድረ ገጽ በሰላም መጡ

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በአማራ ክልል ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 48/1992 ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ ተቋቁሟል፡፡ የተቋሙ ተልዕኮ የአማራ ክልልን የግብርና ምርታማነትን በዘላቂነት የሚያሳድጉና ለአደጋ ተጋላጭነትን የሚቋቋም የምርምር ቴክኖሎጂዎችን ማውጣት ነው፡፡

ተልዕኮ

የተቋሙ ግብ የአማራ ክልልን የኢኮኖሚ እድገት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ ነው፡፡

የምንሠራቸው

በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ማለትም በሰብል፣ በእንስሳት፣ በአፈርና ወሃ አጠባበቅ፣ በባዮቴክኖሎጂ፣ በሥነ ምግብ፣ በአየር ለውጥና ሌሎች ዘርፎች የተሻሻሉ የምርምር ተግባራቶችን ማከናወን የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ፣ የተሻሻሉ አሠራሮችን በማጥናት ለአርሶ አደሮች፣ ለግብርና ባለሙያዎች እና ለባለ ድርሻ አካላት በማስተዋወቅና መነሻ ቴክኖሎጂዎችን በማሰራጨት የአማራ ክልል ግብርና ምርታማነትንና ዘላቂነትን ማረጋገጥ፡፡ አርሶ አደሮችን፣ ከፊል አርሶ አደሮች፣ ተመራማሪዎችን፣ እንዲሁም የኤክስቴሽን ሠራተኞችን ማሰልጠንና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማከናወን፡፡ አገር አቀፍና አለም አቀፍ የፕሮጀክት ትብብሮችን በማድረግ ልምዶችን፣ ኃብቶችንና ዕውቀቶችን በማደራጀት ለግብርና ምርምርና ልማት እድገት ጉልህ ሚና መጫወት::

አስተዋጽዖዋችን

ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ለክልሉ ግብርና የላቀ አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡ በምርምር ተግባራቶቹ የተሻሻሉ የሰብል ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ፣ ዘላቂነት የአስተራረስ ዘዴዎችን በማስተዋወቅ፣ በሽታና ተባይ የመከላከያና መቆጣጠሪያ ዘዲዎችንና ስልቶችን በማውጣት ተግባር ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡

ይቀላቀሉን

ይህንን ድረገጻችንን በመቃኘት የምርምር ተግባራቶቻችንን፣ ፕሮጀክቶቻችንን፣ የምርምር ግኝቶቻችንን እንዲሁም ለግብርናው ዘርፍ የነበሩንን አበርክቶዎች ይጎብኙ፡፡ አርሶ አደር፣ ተመራማሪ፣ ተማሪ ወይም የግብርና ባለድርሻ ከሆኑ በልዩ ልዩ መንገድ ከተቋማችን ጋር አብረው መሥራት ይችላሉና ያግኙን፡፡


ድረገጻችንን ስለጎበኙ እናመሰግንዎታለን፡፡ በጋራ ሆነን በዘላቂነት ግብርናን እንዲዘምን በማድረግ ሕብረተሰባችንን ተጠቃሚ እናድርግ!

ARARI-Footer
ARARI-Footer